TOC

This article is currently in the process of being translated into Amharic (~99% done).

Getting started:

Introduction

ወደዚህ የ C # አጋዥ ስልጠና እንኳን ደህና መጣችሁ፣ የ. NET መሰራትን (መተዋወቅን) በመጠቀም፣ Microsoft አዲስ ቋንቋን C # (C Sharp) የተባለውን አካቷል። C # የተነደፈ ቀላል፣ ዘመናዊ፣ አጠቃላይ ጠቀሜታ፣ ዒላማ-ተኮር የሆነ የፕሮግራም ቋንቋ፣ ቁልፍ የሆኑ ጽንሰቶችን ከሌሎች በርካታ ቋንቋዎች በተለይም ጃቫን በመዋስ የተዘጋጀ ነው።

C # በንድፈ ሀሳብ ከኮምፒውተር ኮድ ጋር ሊቀናጅ ይችላል። ነገር ግን በእውነታው አለም ሁልጊዜ ከ .NET መዋቅር ጋር ይጣጣማል። ስለዚህም በ C # የተጻፉ መተግበሪያዎች(Applications) መተግበሪያውን በሚያስኬደው ኮምፒዩተር ላይ የ .NET መዋቅር መጫን ያስፈልገዋል። የ .NET መዋቅሮች ሰፋ ያለ ቋንቋዎችም ለመጠቀም እንዲችል ያደርጉታል። C # ን አንዳንድ ጊዜ እንደ THE .NET ቋንቋ ይጠቀሳሉ፤ ምናልባትም ከዐውደ ቀመር ጋር አንድ ላይ ስለተሰራ ሊሆን ይችላል።

C # እሴት ፈላጊ ቋንቋ (Object Oriented language) ሲሆን ሁሉን አቀፍ ተለዋዋጭ ወይም ተግባራትን አያቀርብም። ሁሉም ነገሮች በመደብሮች (classes) ውስጥ ይጠቀሳሉ። እንደ int እና string ያሉ ቀላል አይነቶች እንኳን ሳይቀሩ ከ System.Object class ይወርሳሉ።

በቀጣዮቹ ምዕራፎች ውስጥ ስለ C # በጣም አስፈላጊ በሆኑ ርእሶች ይመራሉ።